Skip navigation
st. Mary's University Institutional Repository St. Mary's University Institutional Repository

Please use this identifier to cite or link to this item: http://hdl.handle.net/123456789/2671
Title: በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በክረምት መርሃ ግብር ለሚማሩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሁፍ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች “የምርምር ዘዴ” በሚል ርእስ የተዘጋጀ የርቀት ትምህርት ሞጁል ግምገማ
Authors: ታደሰ, መንግስቱ
Keywords: የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት፤ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሁፍ ትምህርት፤ የርቀት ትምህርት ሞጁል ግምገማ
Issue Date: 2015
Publisher: ST.MARY'S UNIVERSITY
Abstract: የዚህ ጥናት ዋና አላማ ለመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሁፍ ትምህርት ክፍል የክረምት ተማሪዎች “የምርምር ዘዴ“ በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ የቀረበውን ሞጁል የተለያዩ ምሁራን ካቀረቧቸው ንድፈ ሀሳቦች አኳያ አዘገጃጀቱ ምን እንደሚመስል መገምገምና መተንተን ነው፡፡ የጥናቱ ዘዴ መሰረት ያደረገው በገላጭ የምርምር ዘዴ ውስጥ ተካቶ የሚገኘውን የይዘት ትንተና (content analysis) ስልትን ነው፡፡ በዚህ ስልትም በአላማው ስር የሚገኙ የምርምር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስችል ዘንድ የተለያዩ ምሁራን ያቀረቧቸውን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ ለጥናት የተመረጠውን የርቀት ትምህርት ሞጁል ለመፈተሸ ተሞክሯል፡፡ የጥናቱ ውጤትም የሚያመለክተው ተማሪዎች ኮርሱን ተምረው ሲያጠናቅቁ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ባላወቁበት ሁኔታ ወደ ትምህርቱ እንደገቡ መደረጉ (አጠቃላይ አላማ አለመኖሩ) በሌላም በኩል ዝርዝር አላማዎች በአብዛኛው ግልጽነት የጎደላቸው፣ በቀላሉ የማይለኩና ለትግበራ የሚያስቸግሩ ከመሆናቸውም ባሻገር ሰዋሰዋዊ ግድፈትም የበዛባቸው ናቸው፡፡ በሌላም በኩል ይዘቶቹ ቅደም ተከተላቸውን ያልጠበቁ እና መሰረታዊ የሆኑ የምርምር ጽንሰ ሀሳቦችን ከእነማብራሪያቸው ያላካተቱ እንዲሁም በመልመጃዎች፣ በተለያዩ ልምዶችና ማስረጃዎች ባለመደገፋቸው ተማሪዎችን በርቀት ለማስተማር የማስቻል አቅማቸው ዝቅተኛ መሆኑ ተስተውሏል፡፡ በመጨረሻም ተማሪዎች ለርቀት ትምህርት ተብሎ የተዘጋጀውን ሞጁል በሚያነቡበት ጊዜ ልምዱንና እውቀቱን ከቀረቡት ይዘቶች ጋር አጣምሮ፣ በምሳሌዎችና በማስረጃዎች እያስደገፈ የሚያስተምራቸው አካል እንዳለ እንዲሰማቸው አድርጎ ያለማቅረቡ ሁኔታ እንደ ሰፊ ክፍተት ታይቷል፡፡
URI: http://hdl.handle.net/123456789/2671
Appears in Collections:The 4th Annual Open and Distance Education Seminar

Files in This Item:
File Description SizeFormat 
Mengistu.pdf184.24 kBAdobe PDFView/Open
Show full item record


Items in DSpace are protected by copyright, with all rights reserved, unless otherwise indicated.