Skip navigation
st. Mary's University Institutional Repository St. Mary's University Institutional Repository

Please use this identifier to cite or link to this item: http://hdl.handle.net/123456789/2730
Title: Vol. 9, No.1: የሰበር ሰበርና ተግዳሮቶቹ በIትዮጵያ
Authors: Redaei, Mehari
Keywords: ሰበር፤ የሰበር ሰበር፤ የክልል ጉዳይ፤ የፌዴራል ጉዳይ፤ ሕገ መንግሥት፤ የመጨረሻ ውሳኔ፤ መሠረታዊ የሕግ ስህተት፤ የፌዴራልና የክልል የሥልጣን ክፍፍል፤
Issue Date: Sep-2015
Publisher: St. Mary's University
Abstract: በፌዴራልና በክልል የሥልጣን ክፍፍል ማEቀፍ ውስጥ የወንጀል፤ የጉምሩክ፤ የንግድና የAሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን የሚመለከቱ ጉዳዮች በፌዴራል መንግሥት የሥልጣን ክልል ሥር የሚገኙ በመሆናቸው በፌዴራሉ ሰበር ሰሚ የሚመረመሩ ናቸው፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት የEለት ተEለት የውል፤ የቤተሰብ፤ የውርስና የመሳሰሉት ጉዳዮች ግን የክልል ጉዳዮች ስለሆኑ የፍትሕ Aስተዳደራቸው በክልል የዳኝነት ሂደት ላይ ሊያበቃ ይገባል፡፡ ይሁን Eንጂ የክልል ፍርድ ቤቶች የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ተክተው ያስተናገዱዋቸውን የፌዴራል ጉዳዮችም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣናቸው በሰበር ጭምር Aይተው የመጨረሻ Eልባት የሰጡባቸውን ክልላዊ ጉዳዮች የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በAሁኑ ወቅት ዳግም Eያከራከረ ይገኛል፡፡ የክልል ሥልጣን በሆነ ጉዳይ፣ የክልል ሕግን መሠረት በማድረግ የክልል ፍርድ ቤቶች የዳኙትንና በክልል ሰበርም ጭምር Aይተው የመጨረሻ ውሳኔ የሰጡበትን ጉዳይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት Eያስቀረበ ማከራከሩ፣ የሕገ መንግሥቱን ቃላትና መንፈስ መሠረት ያላደረገ፣ Eንዲሁም በሕግ ያልተደገፈ መሆኑን ማሳየት የዚህ ጽሁፍ ዋነኛ ጭብጥ ነው፡፡ ይህ Aሠራር ይልቁንም የፌዴራል ሕገ መንግሥቱ ያደራጀውን የፌዴራልና የክልሎች የዳኝነት የሥልጣን ክፍፍል ተፈጻሚነት Aጠያያቂ የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን የሰበር ሰሚ ችሎቱንም ወደማይወጣው የጉዳዮች ጫና ውስጥ ስለሚከተው ውጤታማነቱን በEጅጉ Eንደሚቀንሰው ጽሁፉ ያሳያል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ Aቅሙንና ጊዜውን በEጅጉ በሚሻሙና በAመዛኙ Aካባቢያዊ (local) በሆኑ ጉዳዮች መጠመዱ የግብAት ብክነትን ይፈጥርበታል፡፡ የክልል ጉዳያቸውን በራሳቸው ለመዳኘት ክልሎች ባላቸው ሥልጣን ውስጥ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት Eንዳይገባ (hands-off) ጽሁፉ ይጠይቃል፡፡ ይልቁንም የፌዴራሉ የመጨረሻ የዳኝነት Aካል የክልል ጉዳዮችን በሰበር በመከለስ ዝርዝር ጉዳይ (micro-management) ሳይጠመድ፣ የክልሎች የዳኝነት Aቅም የሚዳብርበትን Aቅጣጫ ቢቀይስና በዚሁ የAቅም ግንባታ ሥራ ላይ ቢያተኩር Aመርቂ ውጤት Eንደሚገኝ ጽሁፉ ይጠቁማል፡፡
URI: http://hdl.handle.net/123456789/2730
Appears in Collections:Mizan Law Review

Files in This Item:
File Description SizeFormat 
Mehari Redae.pdf349.29 kBAdobe PDFView/Open
Show full item record


Items in DSpace are protected by copyright, with all rights reserved, unless otherwise indicated.